መደበኛ ያልሆነ

ሰኔ 20፤2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በህንድ አንድ የ70 ዓመት አዛውንት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ካለፉ በኃላ የቀብር አስክሬናቸው የያዘው የመቃብር ሳጥን በአፈር መቆፈሪያ ተሽከርካሪ ኤክስካቫተር መጓጓዙ ቁጣን ፈጠረ።ድርጊቱ ክብረ ነክ ነው በሚል በፓርዲሽ ግዛት ሁለት የመንግስት የስራ ሀላፊዎች ከስራ ታግደዋል።

~ በስፔን የማድሪድ ሰማይ ላይ ሰውአልባ አውሮፕላን በመጠቀም ለ10 ደቂቃ ያህል ለኮሮና ቫይረስ ተጎጂዎች ተስፋ እና ለህክምና ባለሙያዎች ጀግኖች የሚል መልዕክት ተላለፈ።የኤልኢዲ እና መተግበሪያ ሶፍትዌር በማበልፅግ እውን ሆኗል።

~ የሰርቢያ የመከላከያ ሚንስትር አሌክሳንደር ቩሊን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ተሰማ።ሚንስትሩ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በመሆን በራሺያ ሞስኮ የጀግኖች ቀን በዓል ላይ በዚሁ ሳምንት ታድመው ነበር።የሰርቢያ ፕሬዝዳንት ቩቺ ከራሺያ አቻቸው ፑቲን ጋር ተገናኝተው የነበሩ ሲሆን የሚንስትሩ መያዝ በፕሬዝዳንቶቹ ላይ ስጋት ፈጥሯል።

~ በግብፅ በዛሬው እለት መስጊዶች ከሶስት ወራት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ክፍት ተደረጉ።የአርብ የጁማ ስነስርዓት ላይ ግን ማሻሻያ ሳይደረግ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። ከ62ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን የ2,620 ሰዎች ህይወት አልፏል።

~ በአሜሪካ እስከ ቀጣዩ ዓመት ግንቦት ወይም ሰኔ ወር ድረስ ትምህርት ቤቶች ላይከፈቱ እንደሚችሉ የጤና ባለሙያዎች ተናገሩ።ጣልያን በበኩሏ በመስከረም አጋማሽ ትምህርት ቤቶችን ትከፍታለች።

~ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ማይክሮሶፍት የችርቻሮ ሱቆቹን ሊዘጋ ነው።

~ በይርግዚስታን ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት የሚሰሩ ተጨማሪ 9 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን ተከትሎ በጽህፈት ቤቱ የሚሰሩ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 17 ከፍ ብሏል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *