መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 20፣2012-ሳዑዲ አረቢያ 48 ሚሊዮን ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅን በበርሜል ሰርቃኛለች ስትል የመን ተናግራለች

የየመን የነዳጅ እና የማዕድናት ሚኒስትር አህመድ ዳሪስ እንደተናገሩት ፤ ሳዑዲ እና አጋሮቿ በ 2018 ዓመት 18ሚሊየን ያልተጣራ ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል በ2019 29.5 ሚሊየን በርሜል ነዳጅ ተሰርቄያለው ስትል የመን ተናግራለች፡፡

በስርቆት ከሳዑዲ አረቢያ በተጨማሪ የተባበሩት አረብ ኤምሬትም ተወንጅላለች፡፡

በ 2018 ዓመት ሳዑዲ አረብያ ከየመን የወሰደችው ነዳጅ በገንዘብ ሲተመን 1.25ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደሚያወጣ ተተምኗል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ በየመን ምድር የወሰደችው ነዳጅ በአንዳንድ ነጋዴዎች አመቻችነት መሆኑ ተገልጿል፡፡

በየእለቱ በየመን ከአስቸኳይ ጊዜ የህክምና ግልጋሎት ጋር በተያያዘ በሃይል እጥረት የ 500 ሰዎች ህይወት ሊያልፍ እንደሚሻል የየመን የጤና ሚኒስትር አብዱልካሪም አል ናሃሪ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *