መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፣2012-አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሊቀ መንበርነታቸው ተነስተው በአቶ አራርሶ ቢቂላ እንዲተኩ ተደርጓል የተባለው የሀሰት ወሬ ነው!

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከመኖሪያ ቤታቸው እንዳይወጡ ተደርገዋል የሚለውን ዜና ተከትሎ ፤ በግንባሩ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው የድርጅቱ አመራሮች ስብሰባ “ሊቀ መንበሩን ለማንሳት ነው” የሚል መረጃ እንዲሰራጭ ምክንያት ሆኖ ነበር።

የግንባሩ አመራር ለሁለት የመከፈሉ ጉዳይ መነጋገሪያ ከመሆኑ በተጨማሪ አቶ ዳውድ ኢብሳ ከሊቀ መንበርነታቸው ተነስተው በአቶ አራርሶ ቢቂላ እንዲተኩ ተደርጓል የሚል ወሬም በስፋት ሲነገር ቆይቷል።

ይሁን እንጂ አቶ ዳውድ ኢብሳን እንዲተኩ ተመርጠዋል የተባሉት አቶ አራርሶ ቢቂላ ዜናው ፍጽም ሐሰት ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

አቶ አራርሶ ትናንት በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ምርጫ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና የነበረው መሆኑን በመናገር አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *