መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፣2012-ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ችሎት አራዳ ምድብ ዛሬ ቀርበዋል

ፖሊስ የደረሰበት ሁኔታ አጠቃላይ ለፍርድ ቤቱ አቅርቧል ፤ ምስክሮች ቃልም ተደምጧል።

ከወንጀሉ ጋር ተያያዥነት አላቸው የተባሉ እቃዎች ለምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ፣ ለፎረንሲክ እንዲሁም ለብሄራዊ ደህንነት ልኬያለሁ ውጤቱን እየተጠባበቅሁ እገኛለሁ ብሏል።

በተጨማሪም የንብረት ግምት ፣ የአስከሬን ምርመራ ውጤት እንዲላክልኝ ለሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ልኬያለሁ ስለዚህ እነዚህ ተጨማሪ ስራዎች ስለሚቀሩኝ ተጨማሪ 14ቀን ቀነ ቀጠሮ ይሰጠኝ የሚል አቤቱታ አቅርቧል።

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በጠበቃቸው በኩል ያቀረቡት መከራከሪያና የፍርድ ቤቱን ቃል በሚመለከት ጠበቃ አዲሱ ከዶቼ ቨለ ጋር በነበራቸው ቆይታ ፤ ባለፈው ችሎት ተጠርጣሪው ከወንጀሉ ጋር ያላቸውን ቁርኝት ፓሊስ አጥርቶ እንዲያቀርብ ነበር የታዘዘው ብለዋል።

“የ 14 ሰው ህይወት አልፏል እንዲሁም ንብረት ወድሟል ውጤት እጠብቃለሁ” ከሚለው ባለፈ ተጠርጣሪው ከወንጀሉ ጋር ያላቸው ግንኙነት አልተገለፀም። ከዚህ ቀደም የወሰደው ቀናት በቂ ነው ዛሬውኑ መዝገቡ ተዘግቶ ደንበኛዬ በነፃ ይሰናበቱ የሚል አቤቱታ ጠበቃ አዲሱ አቅርበዋል።

ፍርዱ ቤቱ የመርማሪ ፖሊስና የተጠርጣሪው ቃል ካደመጠ በኋላ እንዲጨመር የተጠየቀው ቀን አስፈላጊነት ለመወሰን ለፊታችን አርብ ሃምሌ 24 ቀነ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *