መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 21፣2012-ከወሊድ ጋር በተያያዘ ፤ በኢትዮጵያ በቀን 30 እናቶች ህይወታቸው ያልፋል

በጤና ሚኒስቴር የእናቶችና ሕጻናት ጤና አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ ዘነበ አካለ እንደተናገሩት ፤ በ2013 በጀት ዓመት የእናቶችና ህጻናት አገልግሎትን የተሻለ ለማድረግ የወሊድ አገልግሎት ለሚሰጡ የጤና ባለሙያዎች ተገቢና ተከታታይነት ያለው ትምህርትና ስልጠና ይሰጣል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የእናቶችና ህጻናትን ሞት 72 ከመቶ በመቀነስ ከአፍሪካ የተሻለች አገር መሆኗን በመጠቆም ፤ የጨቅላ ህጻናትን ሞት ለመቀነስ ከተቀመጠው ግብ አንጻር ግን አሁንም ክፍተት መኖሩን ጠቁመዋል።

ከወሊድ ጋር በተያያዘ በኢትዮጵያ በቀን 30 እናቶች እንደሚሞቱ የገለጹት አቶ ዘነበ ፣ ይህን ለመቀነስ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ በማያደርግ መልኩ የእናቶችና ህጻናት ፣ የቅድመና ድህረ ወሊድ እንዲሁም የወሊድ አገልግሎቶች በጤና ተቋማት መሰጠታቸው እንዲቀጥሉ እየተደረገ መሆኑን አመልክተዋል።

እንደ ጤና ሚኒስቴር መረጃ ከሆነ በአገሪቱ በየዓመቱ 3 ነጥብ 3 ሚሊዮን ነፍሰጡር እናቶች ይወልዳሉ። ከእነዚህ መካከልም 1 ነጥብ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ከጤና ተቋማት ውጪ ያለህክምና ባለሙያ ድጋፍ የሚወልዱ ናቸው፡፡

ሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *