መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 22፣2012-በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠ

የፌዴራል የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት በአቶ ጃዋር መሐመድ ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ በማየት 12 ቀን ፈቅዶ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ሁከት እና ብጥብጥ በተከሰተባቸው የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች የተሰማራው የምርመራ ቡድን በርካታ የሰው ሞት እና የንብረት ውድመት የተመለከተ መረጃ መላኩንም ፖሊስ ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።

አቶ ጃዋር በበኩሉ የተከሰተው ወንጀል እሱን እንደማይመለከት እና ሚዲያዎች ችሎቱን እንዳይዘግቡ ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ተጠርጣሪው አቶ ጃዋር ያቆማቸው 9 ጠበቆች የምርመራ ሥራው አዲስ አለመሆኑንና ፖሊስ የጠየቀው የጊዜ ቀጠሮ ውድቅ እንዲሆን ወይም ጥቂት ቀን እንዲሆንም ጠይቀዋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ቀደም ሲል በተሰጠው 13 ቀናት ውስጥ ምርመራውን በአግባቡ በማከናወኑ እና ቀሪ ሥራዎችን ለማጠናቀቅ የጠየቀውን ተጨማሪ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ አይቶ 12 ቀን በመፍቀድ ለነሐሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *