መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 22፣2012-ዓመታዊው የሀጅ ጉዞ በዛሬው እለት በሳዑዲ አረቢያ ይጀመራል

በመላው አለም ከፍተኛ የጤና ስጋት የሆነውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ተከትሎ ሳዑዲ አረቢያ ለአለም ዓቀፍ የመካ ተጓዦች ድርበሯን ዝግ አድርጋለች፡፡

በመካ ጉዞ ዘንድሮ መሳተፍ የሚችሉት በሳዑዲ አረቢያ የሚገኙ የሀገሪቱ እና ሌሎች ዜጎች ነዋሪዎች ብቻ ስለመሆናቸው ሳዑዲ አስታውቃለች፡፡

በየዓመቱ 2ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች የሀጅ ጉዞ ያደርጉ የነበረ ሲሆን በተያዘው ዓመት ከ10ሺህ እንደማይበልጡ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡

ተጓዦች በስፍራው ሲደርሱ የሙቀት ልኬት እና የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

ሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ጥላ የነበረውን አስገዳጅ ህግ አንስታለች፡፡

ከ270ሺህ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁባት 3000 የሚጠጉ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው ማለፉን የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ያሣያል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *