መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 27፣2012-በኢራን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ሪፖርት ከተደረገው በሶስት እጥፍ እንደሚበልጥ ተነገረ

የቢቢሲ የፐርሺያ የዜና አገልግሎት በሰራው የምርመራ ዘገባ በኮሮና ቫይረስ ሕይወታቸውን እንዳጡ በኢራን የጤና ሚኒስቴር ሪፖርት ከተደረገው በሶስት እጥፍ እንደሚበልጥ ማረጋገጥ ችለናል ሲል ጽፏል፡፡

ኢራን መረጃውን ለመሸሸግ የፈለገችው እ.ኤ.አ በ 1979 የነበረውን አብዮት እና የፓርላማ ምርጫ ለማካሄድ በሚል የቫይረሱን ስርጭት በመንግስት ትኩረት ሣይሰጠው ቀርቷል፡፡

በኢራን የጤና ሚኒስቴር በኩል በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 17ሺ የበለጠ አይደሉም ቢልም ቢቢሲ 42ሺ ሰዎች በኢራን በቫይረሱ ህይወታቸው አልፏል ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *