መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 27፣2012-በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ በደረሱ የትራፊክ አደጋዎች ፤ የ 4 ሰው ሕይወት ሲያልፍ ከ2ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል

ከሀምሌ 19 ቀን እስከ ሀምሌ 25 2012 ዓ.ም ድረስ ባጋጠሙ የትራፊክ አደጋዎች የ4 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ 6ሠዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት እንዲሁም 15 የንብረት ውድመት አጋጥሟል፡፡ይህም በገንዘብ ሲተመን ከሁለት ሚሊየን 750 ሺ ብር በላይ አንደሚገመት ተጠቁሟል፡፡

አደጋዎቹ በምዕራብ አርሲ አዳባ ፣በምዕራብ ሸዋ ደንዲ እና በምራብ አርሲ ነገሌ አርሲ ወረዳዎች የደረሱ ናቸው፡፡

በተጨማሪም በምዕራብ ሀረርጌ ጡሎ ፣ ምስራቅ ሸዋ አዳአ ቱሉ እና በምዕራብ አርሲ ሻሸመኔ ወረዳዎች አደጋዎቹ ደርሰዋል፡፡

የአደጋው ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር አንፃር የቀነሰ ሲሆን ፤ የአደጋዎቹ መንስኤዎች የጥንቃቄ ጉድለት ነው ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት እና ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር አደጋው እንዲባባስ ምክንያት መሆኑን የኦሮሚያ ፖሊስ የትራፊክ ደህንነት እና ቁጥጥር ክፍል ባለሙያ ሳጅን የባሌወርቅ ደጀኔ ለብስራት ሬዲዮ መናገራቸውን የዘገበችው

በሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *