መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 27፣2012-ሀሪኬን ኢሳያስ የተሰኘዉ ወጀብ እና ከባድ አዉሎ ንፋስ ጉዳት ማስከተሉን ቀጥሏል

ከካሪቢያን ደሴቶች መነሻዉን ያደረገዉ እና የሁለት ሰዎችን ህይወት የቀጠፈዉን ኢሳያስ በካሮላይና የባህር ዳርቻ አካባቢዎች ከባድ አዉሎ ንፋስ እየተመዘገበ ይገኛል፡፡

የንፋሱ መጠን 120 ኬ.ሜ በሰዓት እንደሆነ ተገልጿል፡፡በተያዘዉ 2020 ካጋጠመዉ ወጀብ እና አዉሎ ንፋስ ኢሳያስ የሚል ስያሜ የተሰጠዉ ዘጠነኛዉ ነዉ፡፡ብሄራዊ የሀሪኬን ማዕከል ኢሳያስ ከባድ ዝናብ የሚጥል ሲሆን የወንዞች ከግድብ አልፎ መፍሰስ ሊያስከትል እንደሚችል ተጠቁሟል፡፡

በሰሜን ምስራቃዊ ካሮላይና እና በደቡብ ሰሜናዊ ካሮላይና ለህይወት አስጊ ሊሆን እንደሚችል ማዕከሉ አስጠንቅቋል፡፡በዶምኒክ ሪፐብሊክ እና ፖርታ ሪኮ ኢሳያስ የሚል መጠሪያ በተሰጠዉ ወጀብና አዉሎ ንፋስ ቢያንስ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *