መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-ሊባኖስ በነገው እለት ብሄራዊ የሀዘን ቀን አውጃለች

በሊባኖስ መዲና ቤይሩት በደረሰ ፍንዳታ በርካቶች ሲቆስሉ ከፍተኛ ንብረት ወድሟል።

እስካሁን የፍንዳታው መንስኤ ያልተገለፀ ሲሆን በተጓጂዎቹ ሆስፒታሎች ተጨናንቀዋል።

እንደ ሬውተርስ ዘገባ ከሆነ ከፍርስራሽ ስር 10 አካላት ወጥተዋል። ይሁንና በዉል የሟቾቹንና የተጎጂዎቹ ቁጥር ይፋ አልሆነም።

ፕሬዚዳንት ሚቼል አዉን በባብዳ ቤተመንግሥት ከመከላከያ አባላቱ ጋር አስቸኳይ ስብሰባ ካደረጉ በኋላ በሀገሪቱ በነገው እለት ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲታወጅ ታዟል።

በሊባኖስ የፖለቲካ ውጥረቱ የቀጠለ ሲሆን በተለይ 1975-1990 የእርስ በርስ ጦርነት ወዲህ አሁን የታየው የሀገሪቱ ኢኮኖሚ መሽመድመድ ዜጎችን ክፏኛ እያስቆጣ ይገኛል።

በድንበር አካባቢም ከእስራኤል ጋር ውጥረት ላይ ናቸው።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *