መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-በሙስና ቅሌት ሲብጠለጠሉ የቆዩት የስፔን የቀድሞ ንጉስ ሀገር ለቀዉ ሊሰደዱ መሆኑ ተሰማ

የ82 ዓመቱ ጁአን ካርሎስ ለወንድ ልጃቸዉ ንጉስ ፊሊፔ በጻፉት ደብዳቤ መሰረት የስፔን አቃቢ ህግ ሲፈልጋቸዉ እንደሚገኙ ለአሁኑ ግን ስፔንን ለቆ መዉጣት አማራጫቸዉ ማድረጋቸዉን ገልጸዋል፡፡

ጁአን ካርሎስ በፈጣን የባቡር ግንባታ ጋር በተያያዘ የሙስና ቅሌት ከሳዑዲ አረቢያ ጋር ስማቸዉ ተያይዞ ይነሳል፡፡የስፔን ኩባንያ የመካ መዲና የፈጣን ባቡር ግንባታ የስድስት ቢሊየን ፓዉንድ ዉል ሲያስር የሲዉስ ባንክ ተሳትፎ ነበር፡፡

በስዊስ ባንኩ ተሳትፎ ዙርያ ግልጽ ያልሆኑ መረጃዎች እንዳሉ የማጣራት ሂደቱ መቀጠሉን የስፔን የጸረ ሙስና ባለስልጣናት በመናገር ላይ ይገኛሉ፡፡የስፔን መንግስት ለንጉስ ሆነ ለማንም ፍትህ እኩል ነዉ ሲል በጉዳዩ ዙርያ መረጃ ሰጥቷል፡፡

ከስድስት ዓመት በፊት ንግስናቸዉን ለልጃቸዉ አሳልፈዉ የሰጡት ጁአን ካርሎስ በስፔን የዲሞክራሲ ግንባታ ዉስጥ ከፍተኛ ሚና አላቸዉ፡፡አምባገነኑ ፋሺስታዊ ጄነራል ፍራንሲስኮ ፍራንኮ ከስልጣን ከተወገደ ከሁለት ቀናት በኃላ የቀድሞ ንጉስ ካርሎስ ወደ መንበሩ መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *