መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-ባለፉት 11 ቀናት ውስጥ ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

ባለፉት አሥራ አንድ ቀናት (ከሐምሌ16-27/2012) ከ46 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልዩ ልዩ የኮንትሮ ባንድ ዕቃዎች ከሀገር ለማስወጣት እና ወደ ሀገር ለማስገባት ሲሞከር በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞችና በየደረጃው ባሉ የፀጥታ አካላት በተለያዩ የጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ከዚህ ውስጥ 9.2 ሚሊዮን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ስማርት ስልኮች በሞያሌ እና በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲሁም 8.2 ኪ.ግ የሚመዝን የብር ጌጣጌጥ እና 1500 ኪ.ግ መጠን ያለው ካናቢስ ተብሎ የሚጠራ አደንዛዥ ዕፅ ሞያሌ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሚሌ የመቆጣጠሪያ ጣቢያ ደግሞ 9.2 ሚሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ልባሽ ጨርቆችና ሺሻ ተይዘዋል፡፡
የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የምግብ ዘይት፣ ሲጋራ፣ መድኃኒት በሌሎች የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች የተያዙ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ናቸው፡፡
ኮምቦልቻ፣ ጋላፊ፣ ሑመራ፣ ያቤሎ፣ ድሬዳዋ፣ አዳማ፣ ጅግጅጋ እና ቦምባስ ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ከተያዙባቸው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችና የመቆጣጠሪያ ጣቢያዎች ይገኙበታል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ግምታዊ ዋጋ ያልወጣላቸው በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ሀገር የገቡ ተሽከርካሪዎች እና ከሀገር ሊወጣ የነበረ ቡና ተይዘዋል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የጉምሩክ ሰራተኞችና በየደረጃው ከሚገኘው የጸጥታ መዋቅር ጋር በቅንጀት በሰሩት ስራ መሆኑን ሚኒስቴሩ ባደረሰን መረጃ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *