መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-እስራኤል በጎላን ተራራ ላይ ጥቃት ተሰነዘረ በሚል የአጸፋ ምላሽ በሶርያ የጦር ሰፈር ላይ ሰጠች

በሶርያ መዲና ደማስቆ አቅራቢያ ላይ በሚገኝ የጦር ሰፈር ላይ የእስራኤል አየር ሀይል እርምጃዉን መዉሰዱን የሶርያ መንግስት አሳዉቋል፡፡ባሳለፍነዉ እሁድ በእስራኤል ይዞታ ስር በሚገኘዉ የጎላን ተራራ ግዛት ዉስጥ አራት ግለሰቦች ጥቃት ለመሰንዘር ፈንጂ ሲያጠምዱ የእስራኤል የመከላከያ ሀይል እንደያዛቸዉ መናገሩ አይዘነጋም፡፡

በትላንትናዉ እለት የተሰነዘረዉን ጥቃት ተከትሎ ቦዩካማል በተባለች ከተማ 15 ሰዎች መገደላቸዉን የሶርያ የሰብዓዊ መብት ታዛቢ ቡድን ይፋ አድርጓል፡፡እስራኤል ከሁለት ሳምንት በፊት የሂዝቦላን ታጣቂ መግደሏን ተከትሎ በሶርያ እና እስራኤል መካከል ያለዉ ዉጥረት በመካረር ላይ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *