መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

• አሌክሲስ ሳንቼዝ በቋሚነት ኢንተር ሚላንን ሊቀላቀል ስለመሆኑ ይወጡ መረጃዎች ያሳያሉ

• የቀድሞ የባርሴሎና ተከላካይ አልበርት ፌረር ባርሴሎናዎች ከሜሲ ተላቀው በራሳቸው ሊቆሙ ይገባል ሲል አስተያየቱን ሰጠ

• በአርሰናል እና ቼልሲ የሚፈለገው የ24ዓመቱ አልጄሪያዊ የቤንትፎርድ አጥቂ ሰይድ ቤንራሀማ ስለቀጣይ ክለብ ምርጫው ተጠይቆ “አሁን ላይ ማክሰኞ ምሽት ከፏልሀም ጋር ስለሚደረገው የመልስ ጨዋታ ብቻ ነው ሃሳቤ” ሲል ምላሽ ሰቷል

• በውድድር ዓመቱ ለክለቡ ያለውን ሁሉ አበርክቷል ሲሉ ጆሴ ሞሪንሆ ብራዚላዊው ሉካስ ሞራን አወደሱ

• በየእለቱ የዘረኝነት ጥቃት እንደሚደርስበት የቶተንሀሙ ተጫዋች ዳኒ ሮዝ ተናግሯል

• ዊሊያን አሁንም ቼልሲ ያቀረበለትን የሁለት ዓመት ኮንትራት ውድቅ አድርጎታል። ክለቡ እድሜያቸው ከ 30ዓመት በላይ ለሆናቸው ተጫዋቾች ከአንድ ዓመት በላይ ባያቀርብም ለዊሊያን ይህንኑ ማሻሻያ ተግብሮታል።

• አርሰናል ወሳኝ ዝውውሮችን ከፈፀመ ለኦባሚያንግ ኮንትራት ማቅረቡ አይቀሬ ነው። ውይይቶች ቢደረግም እስካሁን በጠረጴዛ ዙሪያ ወረቀት አስቀምጠው አልመከሩም ተብሏል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *