መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 28፣2012-የብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

~ በሊባኖስ መዲና ቤሩት ባጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ቢያንስ የ10 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በፍንዳታው ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚንስትር ሀማድ ሀሰን ተናግረዋል።

~ የፍንዳታው ንዝረት በ240 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ከሊባኖስ በማለፍ በሳይፕረስ ደሴት ነዋሪዎች እንደተሰማቸው ተረጋግጧል።

~ የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ጋቢ አሽኬናዚ እስራኤል በዚህ ፍንዳታ እጇ እንደሌለበት ተናግረዋል።

~ በቤሩት ወደብ አቅራቢያ ከሚገኘው ግዙፍ መጋዘን ከተሰማው ፍንዳታ አስቀድሞ በመጠን በርከት ያሉ አነስተኛ ፍንዳታ ተመዝግቧል።

~ የዛሬው ፍንዳታ የደረሰበት ስፍራ የቀድሞ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚንስትር ራፊክ ሀሪሪ እ.ኤ.አ በ2005 በመኪና ላይ በተጠመደ ቦንብ የተገደሉበት ስፍራ አቅራቢያ ነው።

~ የፍንዳታው ምክንያት ምን እንደሆነ በግልጽ ባይነገርም አንዳንድ ሪፖርቶች ድንገተኛ አደጋ ሊሆን እንደሚችል ተጠቁሟል።

✍️ የሀገራት መሪዎች በፍንዳታው ዙርያ ምን አሉ

~ የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ ጥልቅ የሆነ ሀዘናቸውን በመግለፅ ለተጎጂዎች በቶሎ ማገገም እንዲሆን ተመኝተዋል።

~ ዋይት ሀውስ የሀዘን መግለጫ በማውጣት የትራምፕ አስተዳደር ጉዳዩን በቅርበት ሆኖ እንደሚያጣራ ይፋ አድርጓል።

~ የአውሮጳ ምክርቤት ፕሬዝዳንት ቻርለስ ሚካኤል ከሊባኖስ ጎን በመቆም ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *