መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 29፣2012-አጫጭር መረጃዎች ከቤሩት

~ የማሌዢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሂሻማሙዲን ሁስኒ በሊባኖስ ያጋጠመውን ፍንዳታ ተከትሎ የተሰጣቸውን ሀሰን በመግለፅ በማንኛውም መንገድ እና በፀሎት ከሊባኖስ ዜጎች ጋር ነን ብለዋል፡፡

~ በቤሩት ካጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ ሁለት የፊሊፒንስ ዜጎች ህይወት ሲያልፍ ስድስቱ ደግሞ ክፉኛ ቆስለዋል፡፡ በሊባኖስ ከ 27ሺህ በላይ የፊሊፒንስ ዜጎች በተለያየ የስራ ዘርፍ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡

~ የሊባኖስ የጉምሩክ ቢሮ በቤሩት ካጋጠመው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የቤሩት የወደብ ቢሮ አሙኒየም ናይትሬት ሊያከማቹ ፈፅሞ አይገባም ብለዋል፡፡

~ በቤሩት ያጋጠመው ከባድ ፍንዳታ ተከትሎ በሬክተር ስኬል የተለካ 3.5 የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ አጋጥሞ እንደነበረ የጀርመን ጂኦ ሳይንስ ማዕከል አስታውቋል፡፡

~ የአሜሪካ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ የቤሩት ከተማ ፍንዳታ ልክ የሽብር ጥቃት ዓይነት መልክ ነበረው ብለዋል፡፡ የሊባኖስ ህዝብ ጋር መልካም ወዳጅነት አለን አብረናችሁ ነን ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል፡፡

~ የፍንዳታውን ሁኔታ የሚያጣራ ኮሚቴ በቅርብ ቀናት ምክንያቱን ይፋ እናደርጋለን ብሏል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር ሀሰን ደአብ የተመራ ስብሰባ በባአባዳ ቤተመንግስት ተካሂዷል፡፡

~ 2700 ቶን የሚመዝን አሙኒየም ናይትሬት የደህንነት ሁኔታው ባልተጠበቀ መልኩ ተከማችቶ የነበረ ሲሆን ይህ ዓይነቱ እንዝላልነት ተቀባይነት የለውም ሲሉ ፕሬዝደንት ሚካኤል ኦን ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *