መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 30፣2012-በናይጄሪያ ሀይድሮክሲክሎሮኪዊን መድሃኒት ዋጋ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱ ተሰማ

የናይጄሪያ መንግስት እንዳስታወቀዉ የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነዉ ሀይድሮክሲክሎሮኪዊን ዋጋዉ ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ይፋ አድርጓል፡፡መድሃኒቱ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል እንዲሁም ህሙማን በቶሎ እንዲያገግሙ ያደርጋል የሚል መረጃ መሰራጨቱን ተከትሎ ተፈላጊነቱ ጨምሯል፡፡

የአለም የጤና ድርጅት በበኩሉ የጸረ ወባ መድሃኒት የሆነዉ ሀይድሮክሲክሎሮኪዊን በኮሮና ቫይረስ የሚከሰት ሞትን እንደማይቀንስ በይፋ መናገሩ ይታወሳል፡፡በመረጃ ክፍተት የተነሳ ግን የመድኃኒቱ ዋጋ ማሻቀቡን ቀጥሏል፡፡

ከአራት ወራት በፊት 60 መድሃኒት የሚይዘዉ አንድ እሽግ በ3000 የናይጄሪያ ናይራ ይሸጥ የነበረ ሲሆን አሁን ላይ በመድሃኒት መደብር ዉስጥ በ75ሺ ናይራ በመሸጥ ላይ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *