መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 30፣2012-ቻይና የካናዳ ዜግነት ባለዉ ግለሰብ ላይ የሞት ትዕዛዝ አስተላለፈች

ሹ ዊሆንግ የተባለዉ የካናዳ ዜግነት ያለዉ ግለሰብ በመኖሪያ ቤቱ ዉስጥ ኬታሚን የተሰኘ መድሃኒትን ሲያመርት በመገኘቱ በዛሬዉ እለት የሞት ቅጣት ተላልፎበታል፡፡ይህ መድኃኒት ከባድ ህመምን ለመቀነስ፣ሰዎች ራሳቸዉን እንዲስቱ የሚሰጥ ሲሆን በዚህ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ዉስጥ ከ120 ኪ.ግ በላይ መድኃኒቱ ተገኝቷል፡፡

በቻይና የህገወጥ መድኃኒት ምርትና ሽያጭ ከፍተኛ ቅጣትን የሚያስጥል ነዉ፡፡ይህንኑ ተከትሎ በካናዳዊዉ ግለሰብ ላይ የሞት ቅጣት ብይን ተላልፏል፡፡ሆኖም ግን ቅጣቱን በተመለከተ በቻይና እና ካናዳ መካከል ባለዉ የዲፕሎማሲ ዉዝግብ የተነሳ የአጸፋ ምለሽ ነዉ ሲሉ በርካቶች እየተቹት ይገኛል፡፡

ካናዳ የሁዋዌ ኩባንያ የፋይናንስ ሀላፊ የሆነችዉን ሜንግ ዋንዝሁ በአሜሪካ በወጣ የእስር ትዕዛዝ የተነሳ በቁጥጥር ስር ማዋሏ ቻይናን አስኮርፏል፡፡ቻይና ሌሎች ሁለት የካናዳ ዜጎችን በተለያዩ ጥፋቶች በመወንጀል የሞት ብይን እንደተወሰነባቸዉ ማሳወቋ ይታወሳል፡፡

የቻይና የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ቃልአቀባይ ዋንግ ዊንቢን በበኩላቸዉ የሹ የሞት ፍርድ ከቻይና ካናዳ የዲፕሎማሲ ዉዝግብ ጋር ተያያዥነት የለዉም ብለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *