መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 30፣2012-አጫጭር መረጃዎች ከሊባኖስ ፍንዳታ ጋር በተያያዘ

~ ሊባኖስ የሚገኙት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ለሀገሪቱ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ሲያስታዉቁ ነገር ግን ድጋፍ የሚደረገዉ ገንዘብ በቀጥታ ለተጎጂዎች እንዲዉል ጠይቀዋል፡፡ፈረንሳይ የሊባኖስ ቅኝ ገዢ የነበረች ሲሆን ሊባኖስ በሙስና እና ኢኮኖሚያዊ ቀዉስ ዉስጥ ትገኛለች፡፡

~ የቀድሞ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚንስትር ሰአድ ሀሪሪ በቤሩት የደረሰዉ ፍንዳታ መንስዔ በዓለም አቀፍ ገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥሪ አቀረቡ፡፡በፍንዳታዉ ቢያንስ የ157 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ5000 ያላነሱ ሰዎች ከከባድ እስከ ቀላል የአካል ጉዳት አጋጥሟቸዋል፡፡

~ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያለማረጋገጫ የቤሩቱ ፍንዳታ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ጥቃት ነዉ ሲሉ ተናገሩ፡፡ሀኖም ግን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ዋና ጸሀፊ ማርክ ስፔር ድንገተኛ ፍንዳታ ነዉ ሲሉ ከትራምፕ የተቃረነ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

~ 50 የድንገተኛ ጊዜ እና የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ሊባኖስ የላከችዉ ራሺያ ተጨማሪ ድጋፍን በቀጣዮቹ ጥቂት ሰዓት 3 የረድኤት ድጋፍ የሚያደርግ በረራ ሊባኖስ ቤሩት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

~ የአዉስትራሊያ ጠቅላይ ሚንስትር ስኮቲ ሞሪሰን ለሊባኖስ የምግብና የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ የሚዉል የ1.4 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ሀገራቸዉ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቁ፡፡

~ ኢራቅ ሊባኖስን ሊያጋጥማት ለሚችለዉ የነዳጅ አቅርቦት አስቀድማ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች፡፡ቱርክ በተመሳሳይ የረድኤት ድጋፍ የሚያደርጉ ባለሙያዎቿ ቤሩት ከተማ ደርሰዋል፡፡

~ በቤሩት ወደብ የደረሰዉን ፍንዳታ የሚያጣራዉ ቡድን በአራት ቀናት ዉስጥ ዉጤቱን እንዲያስታዉቅ ትዕዛዝ መተላለፉን የሊባኖስ የዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ቻርቤል ዊቢ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *