መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 30፣2012-አጫጭር ስፖርታዊ መረጃዎች

• ማንችስተር ሲቲ ተጨማሪ አራት ተጫዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋል፡፡ ሴኔጋላዊው የናፖሊ ተከላካይ ካሊዱ ኩሊባሊ(29ዓመቱ)፣አርጀንቲናዊው የኢንተርሚላን አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ(22) እንዲሁም ፖርቹጋላዊው የኳስ አቀጣጣይ ጆአኦ ፊሊክስ(20) ከአራቱ መካከል ናቸው፡፡

• የ28 ዓመቱ የባርሴሎና ተመላላሽ ፊሊፔ ኩቲንሆ ወደ አርሰናል የመጓዝ እድሉ የሰፋ ነው እየተባለ ይገኛል፡፡ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በውሰት በባየር ሙኒክ ማሳለፉ አይዘነጋም፡፡

• አርሰናል ለቼልሲው አማካኝ ዊሊያን (31ዓመቱ) የሶስት ዓመት ኮንትራት አቅርቦለታል፡፡ ከቼልሲ ጋር በኮንትራት የተነሳ ካለመስማማት መድረሳቸው ይታወቃል፡፡

• አርሰናል ብራዚላዊው የሊል ተከላካይ ጋብሪኤል ማጋልሄስ (22) ለማስፈረም ከተፎካካሪዎቹ ማን.ዩናይትድ ፣ ኤቨርተንና ናፖሊ የተሻለ እድል አልው ተብሏል፡፡

• ቼልሲ 60ሚሊዮን ፓውንድ የተለጠፈበትን ኡራጋዊ ተከላካይ ጆሴ ጂሚኔዝ (25) ከአትሌቲኮ ማድሪድ ለማስፈረም ድርድር ላይ ይገኛል፡፡

• ቼልሲ የግራ ተመላላሹ ሰርጂዮ ሬጉሊዮን (23) ከሪያል ማድሪድ ለማስፈረም ከክለቡ ጋር ውይይት ላይ ይገኛል፡፡ተጫዋቹ በውሰት ያለፈውን የውድድር ዓመት በሲቪላ ነው ያሳለፈው፡፡

• የባርሴሎናው ግብ ጠባቂ ማርክ አንድሬ ቴር ስቴገን ተጨማሪ የአምስት ዓመት ውል ከክለቡ ጋር ሊያስር ነው፡፡ የ 28 ዓመቱን ጀርመናዊ ግብ ጠባቂ ለማስፈረም አሰፍስፈው ለሚገኙት ቼልሲዎች ጥሩ የማይባል ዜና ነው፡፡

• ሪያል ማድሪድ ኮሎምቢያዊውን አማካኝ ጄምስ ሮድሪጌዝ (29) በ13.5 ሚሊዮን ፓውንድ ለተቀናቃኛቸው አትሌቲኮ ማድሪድ አሳልፈው ሊሰጡ ይችላል እየተባለ ነው፡፡

• ቶተንሃም 35ሚሊዮን ዩሮ የሚገመተው የቀኝ ተመላላሽ ሰርጂ አውሪየር ለመሸጥ ዝግጁ ናቸው፡፡ የ27ዓመቱ አይቬሪኮስታዊ የግላቸው ለማድረግ ኤሲ ሚላን እና ሞናኮ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል፡፡

• የጀርመኑ ክለብ ዌርደር ብሬመን የማንችስተር ዩናትዱን የ 20 ዓመት ሆላንዳዊ ተስፈኛ ታሂዝ ቾንግ በውሰት ማስፈረም ይሻሉ፡፡

• ክሪስታል ፓላስ ለስኮትላንዳዊው ተጫዋች ሪያን ፍሬዘር ጥያቄ አቅርቧል፡፡ ተጫዋቹ ቦርንመውዝን መልቀቁን ተከትሎ እስካሁን የማንም ንብረት አይደለም፡፡ ወደ ሊጉ ያደገው ፉልሃምም የተጫዋቹ ፈላጊ ነው፡፡

• የቦርንመውዝን የአሰልጣኝነት መንበር የ 42 ዓመቱ ጃሰን ቲንዳል ይረከበዋል እየተባለ ይገኛል፡፡ የክለቡ የቀድሞ አሰልጣኝ ኤዲ ሃዊ ከክለቡ መለያየቱ ይታወቃል፡፡

° ኢንተር ሚላን በሶስት ዓመት ውል በቋሚነት አሌክሲስ ሳንቼዝን (31) ከማንቸስተር ዩናይትድ አስፈርሟል። በ 29 ጨዋታዎች ላይ ተሰልፎ 4ግቦችን ማስቆጠር ችሏል።

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *