መደበኛ ያልሆነ

ሐምሌ 30፣2012-የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በመጥለፍ የተከሰሱ ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በእነ ከሊፋ አብዱረህማን የክስ መዝገብ የደንቢዶሎ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ህዳር 24 እና 25/2012 ዓ.ም በመጥለፍ በሽብር ወንጀል ከተከሰሱት 17 ግለሰቦች መካከል ዘጠኙ የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል።

በሦስት የሽብር ወንጀል የተከሰሱት ተከሳሾቹ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበው የተከሰሱበት ወንጀል ተነቦላቸዋል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ ተከሳሾቹ በበኩላቸው ለፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት መቃወሚያ በጽሁፍ አቅርበዋል።

ከሳሽ ዐቃቤ ህግ በመቃወሚያው ላይ ምላሽ እንዲሰጥና ትእዛዝ ለመስጠት ፍርድ ቤቱ ለነሐሴ 25/2012 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *