መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 1፤2012-በሊባኖስ መዲና ቤሩት ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀስቅሷል

በትላንትናዉ እለት በመንግስት ላይ ተቃዉሞ ያሰሙ ሰልፈኞች ከጸጥታ አካላት ጋር ተጋጭተዋል፡፡በከተማዋ በሚገኘዉ የፓርላማ ህንጻ አካባቢ የተሰበሰቡ ሰልፈኞችን ለመበተን ፖሊስ አስለቃሽ ጋዝ ተጠቅሟል፡፡

በመንግስት ቸልተኝነት የተነሳ በቤሩት ወደብ አካባቢ ለስድስት ዓመታት ተከማችቶ የነበረዉ 2700 ቶን አሙኒየም ናይትሬት ያስከተለዉ ፍንዳታ ቢያንስ የ137 ሰዎችን ህይወት ሲነጥቅ 5000 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

መንግስት ለዚህ ፍንዳታ ተጠያቂ ናቸዉ ሲል 16 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ቢያዉል ዜጎች ግን ቁጣቸዉን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *