መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 1፤2012-በስሪላንካ ምርጫ ወንድማማቾቹ ከፍተኛ ድል ቀናቸው

በስሪላንካ በተካሄደዉ ሀገር አቀፍ ምርጫ ጎታባያ ራጃፓክሳ በምርጫዉን ማሸነፋቸዉን ተከትሎ የፕሬዝዳንት ወንበሩን ሲያስጠብቁ ወንድማቸዉ ማሂንዳ ራጃፓክሳ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ወንበር ይይዛሉ፡፡

የወንድማማቾቹ ፓርቲ የሆነዉ ሲሪላንካ ፒፕልስ ፍሮንት ከ225 የምክርቤት የመቀመጫ ወንበር 145ቱን ማሸነፍ የቻለ ሲሆን የፓርቲዉ አጋር ፓርቲ ተጨማሪ አምስት ወንበሮችን አሸንፏል፡፡

አወዛጋቢ የሆነዉ ይህ ቤተሰብ በመጀመሪያ እ.ኤ.አ ከ2005 እስከ 2015 ድረስ ማሂንዳ ራጃፓክሳ ፕሬዝዳንት የነበሩ ሲሆን ወንድማቸዉ ደግሞ ከ2015 እስከ 2025 በፕሬዝዳንትነት የሚቆዩበትን እድል በማመቻቸት ወንድማማቾቹ ሲሪላንካን እየተቀያየሩ ለ20 ዓመታት መምራት ችለዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *