መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 1፤2012-ከ8ኛና 12ኛ ክፍል ውጭ ላሉ ተማሪዎች የነፃ ዝውውር መደረጉ ትምህርት ጥራት ላይ የሚፈጥረው ችግር እንደማይኖር የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስቴር ከ8ኛ እና 12 ኛ ክፍል ውጭ ያሉ ተማሪዎች ወደ ቀጣዩ ክፍል ካለፈተና እንዲዛወሩ መወሰኑን ተከትሎ የትምህርት ጥራት ላይ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው።

የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) የነፃ ዝውውር መደረጉ ተማሪዎች ላይ የሚፈጠረውን ጫና መንግስት እንዲሸከም በማድረግ ከትምህርት ውጭ የቆዩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ ለማድረግ ታስቦ ነው ብለዋል።

አሁን በምንከተለው ስርዓተ ትምህርት የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥ አንችልም ያሉት ሚኒስትሩ 2014 ላይ ወደ ተግባር የሚገባ ስረዓተ ትምህርት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።

የትምህርት ጥራት ችግርን በዘላቂነት የሚፈታው ይህ ስርዓተ ትምህርት እንጂ ፈተና በመፈተንና ባለመፈተን የሚረጋገት የትምህርት ጥራት አይኖርም ነው ያሉት።

የትምህርት ሚኒስቴር የነፃ ዝውውር ውሳኔን ሲወስን የተለያዩ ሀገራትን ተሞክሮ በመውሰድና በተለያየ ምክንያት
የኮቪድ 19ኝ ወረርሽኝን ተከትሎ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ስለቆዩ በዚያው እንዳይቀሩ ለማድረግ ታስቦም ጭምር ነው።

የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑ ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *