መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፣2012-በኮንታ ልዩ ወረዳ ሰሞኑን በተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ናዳ ተከስቶ የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተገለፀ፡፡

በልዩ ወረዳዉ ሰሞኑን ተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት በጨካ ቦቻ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኮማ መንደር ነሀሴ 3 ከቀኑ ስምንት ሰዓት ገደማ የሶስት ሰዎች ህይወት በናዳ ማለፉን የሟች ቤተሰቦችና የአከባቢዉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።
የወረዳዉ አደጋ ስጋትና አመራር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፊን ጎበዜ በልዩ ወረዳዉ ከሚገኙ ቀበሌዎች 23ቱ ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት ያለባቸዉ መሆኑን ተናግረዉ ከእነዚህም አንዱ በሆነዉ ጨካ ቦቻ ቀበሌ ሰሞኑን ተከታታይ በጣለዉ ዝናብ ምክንያት ናዳ ተከስቶ ዕድሜያቸዉ የ8፣ 10 እና 12 ዓመት የሆኑ ልጆች ህይወታቸዉ አልፏል

በአስከሬን ፍለጋ የሁለቱ ተገኝቶ የተቀበረ ሲሆን የአንዱ አስከሬን ፍለጋ መቀጠሉን የተናገሩት ኃላፊዉ በሌሎችም በተተነበዩ ቀበሌያት መሰል አደጋ እየተከሰተ በመሆኑ ህብረተሰቡ ልዩ ጥንቃቄ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡የልዩ ወረዳዉ ከፍተኛ አመራር አካላትና የፀጥታ አካላት በቦታዉ ተገኝተዉ አስከሬን የማፈላለግ ስራዉ ቀጥሏል፡፡

ልዩ ወረዳዉ ካለዉ መሬት አቀማመጥ መነሻ በተለያዩ ጊዜያት የተፈጥሮ አደጋ እየተመዘገበት ሲሆን በተመሳሳይ በጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም የ22 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *