መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፣2012-ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ወደ አዲስ አበባ ያስገቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ግምታዊ ዋጋቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በተሽከርካሪ በመጫን ወደ አዲስ አበባ ያስገቡ ሁለት ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ህገ-ወጥ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ይዘው የተገኙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው አቦ ሴራ ፒስታ መንገድ ቴሌ ጫፍ አካባቢ ነው።

የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወንጀል መርማሪ ምክትል ሳጅን ማናየ ጫኔ እንደጠቀሱት፥ ተጠርጣሪዎቹ በሲኖትራክ ተሽከርካሪ ከጫኑት 43 ኩንታል ስንዴ ስር 4 ሺህ ኪሎ
ግራም ልባሽ ጨርቅ እና 11 ሺህ 280 የፈረንሳይ ሽቶ አስገብተዋል።

ተጠርጣሪዎቹ በአጠቃላይ የዋጋ ግምታቸው ከ1 ሚሊየን ብር በላይ የሚሆኑ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ደብቀው ወደ አዲስ አበባ ይዞው ሲገቡ ከህብረተሰቡ በደረሰ
ጥቆማ በቁጥጥር ስር ሊውሉ መቻላቸውን አስረድተዋል።

በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝም መግለፃቸውንም ብስራት ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሣያል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *