መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፣2012-የአዲስ አበባ ፖሊስ ጎተራ አካባቢ በሚገኝ አንድ የጋራ መኖሪያ ቤት ውስጥ 108 ህገወጥ ማህተሞች መያዙን አስታወቀ።

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ 108 ማህተሞች እና የተለያዩ ሀሰተኛ ሰነዶችን ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባራት ሲጠቀሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሰር መዋሉን ፖሊስ ገልጿል።

በከተማችን አዲስ አበባ በተለያዩ ጊዚያት ሐሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም ህገ-ወጥ ተግባር ሲፈፅሙ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው በህግ አግባብ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸውን ግለሰቦች የወንጀል ድርጊት መረጃ በመስጠት ህብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መልዕክቶችን ማስተላለፋችን ይታወሳል ፡፡

አሁንም በአንዳንድ አካባቢ መሰል የወንጀል ድርጊቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወርዳ 4 ጎተራ ኮንዶሚኒየም ውስጥ ሀምሌ 1ቀን 2012ዓ. ም ሁለት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የዋሉበት ወንጀልም ይህው ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ 108 የግል እና የመንግስት መስሪያ ቤት፣ 15 ሀሰተኛ ሰነዶችን እንደተገኘባቸው የክፍለ ከተማዉ ፖሊስ መምሪያ ማስተባበርያ ሀላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ስለሽ ሸንቁጤ ተናግረዋል።

ከተጠቀሱት ማህተሞች ውስጥ የትምህርት ሚኒስቴር የሙያ ማረጋገጫ ማሕተም እና የተለያዩ መንግስታዊ ተቋማት ህገወጥ ሰነዶች መገኘታቸውን ፖሊስ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *