መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፤2012-በሆንግ ኮንግ ቱጃሩ ሰው ጂሚ ላ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተሰማ

ጂሚ ላ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው ከውጭ ሃይሎች ጋር በጥምረት ትሰራለህ በሚል የተነሳ ነው፡፡

የ 71 ዓመቱ ቱጃር በሆንግ ኮንግ አስተዳደር የተዘጋጀውን አወዛጋቢውን ብሄራዊ የደህንት ህግ በመተቸት ይታወቃል፡፡

እርሱን ጨምሮ ሰባት ሰዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፖሊስ ይፋ አድርጓል፡፡ የጂሚ ላ እስርን ተከትሎ በዛሬው እለት በሆንግ ኮንግ ውጥረት ነግሷል፡፡

በአልባሳት ኢንዱስትሪ መነሻውን ያደረገው ጂሚ ላ ከ 1ቢሊዮን ዶላር በላይ ሀብትን አካብቷል፡፡

የቻይና መንግስት የራሴ አካል ናት በሚል በሆንግኮንግ የሚያሳርፈው ተፅዕኖ ነዋሪዎችን ማስቆጣቱን ቀጥሏል፡፡

ሆንግ ኮንግ እ.ኤ.አ በ 1997 ከብሪታኒያ ለቻይና ተላልፋ ከተሰጠች በኋላ አንድ ሀገር ሁለት አስተዳደር የሚል ግንኙነትን ከቻይና ጋር ፈጥራ ቆይታለች፡፡

በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *