መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፤2012-በቤላሩስ በትናንትናው እለት የተካሄደውን ፕሬዝደንታዊ ምርጫ ተከትሎ በሀገሪቱ ከፍተኛ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ

በቤላሩስ መዲና ሚኒስክ እና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ተቃውሞ ሊቀሰቀስ የቻለው በቤላሩስ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ በምርጫው ሀገሪቱን ለረጅም ዓመታት የመሩት አልክሳንደር ሉካሼንኮ በድጋሚ መመረጣቸው መገለፁን ተከትሎ ነው፡፡

የቤላሩስ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንዳስታወቀው 80 በመቶ የመራጮችን ድምፅ የወቅቱ የሀገሪቱ መሪ ሉካሼንኮ ማግኘታቸውን ይፋ አድርጓል፡፡

‹‹አይኖቼን ማመን እፈልጋለሁ በርካታ ደጋፊዎች ከእኛ ጋር ነበሩ›› ስትል ትላንትና ማታ ለጋዜጠኞች በሰጠችው መግለጫ አስታውቃለች፡፡

የ37 ዓመቷ ቲክሀኖቫስካይ ወደ ምርጫ ልትገባ የቻለችው በምርጫው ተጠባቂ የነበረው ባለቤቷ በቁጥጥር ስር መዋሉን ተከትሎ ነው፡፡

ሉካሼንኮ ላለፉት 26ዓመት በቤላሩስ የስልጣን መንበሩን ተቆጣጥረው ይገኛል፡፡ በትላንትናው ምርጫ በድጋሚ ማሸነፋቸው ያስቆጣቸው ዜጎች አደባባይ በመወጣት ከፀጥታ አካላት ጋር ተጋጭተዋል፡፡

የተፈጠረው ከባድ ተቃውሞ በሀገሪቱ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በድጋሚ እንዳያገረሽ ስጋት ፈጥሯል፡፡

የ9.5ሚሊዮን ህዝቦች መኖሪያ በሆነችው ቤላሩስ ከ70ሺ ያላነሱ ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ የ600 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ 

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *