መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 4፤2012-በብራዚል በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ100ሺ በላይ ሁኗል

በቫይረሱ በብራዚል ባለፉት 50 ቀናት ብቻ ተጨማሪ 50ሺ ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥርም ከሶስት ሚሊዮን ልቋል፡፡

ቀኝ ዘመሙ የሀገሪቱ ፕሬዝደንት ጄር ቦልሶናሮ ለቫይረሱ የሰጡት ምላሽ ደካማ በመሆኑ የተነሳ ብራዚልን በሽታው ክፉኛ ፈተኗል፡፡

በፕሬዝደንቱ ምላሽ የተበሳጩ ሁለት የጤና ሚኒስትር በተለያየ ጊዜ ስራቸውን መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

በአሁኑ ወቅት የብራዚል የጤና ሚኒስትር በመሆን እየመሩ የሚገኙት የጦር ጄነራል የነበሩና በህብረተሰብ ጤና ዙሪያ ልምድ የሌላቸው ሰው ናቸው፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *