መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 5፣2012-በቤላሩስ ለሁለተኛ ምሽት ከፍተኛ ተቃውሞ ተካሄደ

ቤላሩስን ለ26 ዓመታት የመሩት ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ባሳለፍነዉ እሁድ በተካሄደዉ ምርጫ ከ80 በመቶ በላይ የመራጮችን ድምጽ አግኝተዉ አሸንፈዋል መባሉ ያስቆጣቸዉ ዜጎች በመዲናዋ ሚኒስክ ከፖሊስ ጋር ተጋጭተዋል፡፡

የመንግስት ባለስልጣናት እንዳስታወቁት በእጁ ላይ ተቀጣጣይ ነገር ይዞ የነበረ አንድ ሰልፈኛ የያዘዉ ፈንጂ በመፈንዳቱ ህይወቱ ማለፉን አስታዉቀዋል፡፡ፖሊስ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰልፈኞችን ለመበተን አስለቃሽ ጋዝን ተጠቅሟል፡፡

ባለቤቷ በቤላሩስ መንግስት መታሰሩን ተከትሎ በምርጫዉ ወደ ፉክክር የገባችዉ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዋ ቲካሀኖቭስካይ የምርጫዉን ዉጤት እንደማትቀበል ተናግራለች፡፡በርካታ ሰዎች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑ እየተዘገበ ይገኛል፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *