መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 5፣2012-ቻይና በአሜሪካ ከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብን ጣለች

ከሆንግ ኮንግ ጉዳይ ጋር በማያያዝ ቻይና በ11 አሜሪካውያን ላይ ማዕቀብን የጣለች ሲሆን ከነዚህ መካከል ስድስቱ የህግ አውጪዎች አባላት ስለመሆናቸዉ ተሰምቷል፡፡በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለዉ ዉዝግብ እየተካረረ ይገኛል፡፡

ባሳለፍነው አርብ አሜሪካ የፖለቲካ ነጻነትን አይተገብሩም ባለቻቸዉ የሆንግ ኮንግ አስተዳዳሪ በሆነችዉ ኬሪላም እና በሌሎች አስር የቻይናና የሆንግ ኮንግ የመንግስት ባለስልጣናት ላይ ማዕቀብ መጣሏ አይዘነጋም፡፡

በምላሹ ቻይና የፍሎሪዳ ሴናተር ማርኮ ሩቢዮ፣የቴክሳስ ሴናተር ቴድ ክሩዝ፣የአርካንሰስ ሴናተር ቶም ኮተን፣የፔንስላቫኒያ ሴናተር ፓት ቱሜይ፣የሚሶሪ ሴናተር ጆሽ ሀውሌይ ላይ ማዕቀብን ጥላለች፡፡

ቻይና በዉስጥ ጉዳያችን አሜሪካዉያኑ ባለስልጣናት ከመግባት ይጠንቀቁ ስትል መልዕከት አስተላልፋለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *