መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 5፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

~ በመላዉ ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ20 ሚሊየን በላይ ደርሷል፡፡20,254,685 ሰዎቸ በቫይረሱ ሲጠቁ የሟቾች ቁጥር 738,930 ደርሷል፡፡እንደ ጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ 13,118,618 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

~ በብራዚል ባለፉት 24 ሰዓት 703 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉን ሲያጡ 22,048 ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል፡፡አጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸዉ ያጡ ሰዎች በብራዚል 101,752 ሲደርስ የተጠቂዎች ቁጥር ከ3 ሚሊየን ልቋል፡፡

~ የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተዉ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ዜጎችን የሚከለክል መመሪያ መዘጋጀቱን ይፋ አደረጉ፡፡መመሪያዉ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸዉን ሰዎች የሚመለከት ነዉ፡፡

~ ፓፓዉ ኒዉ ጊኒ በተያዘዉ ሳምንት የኮሮና ቫይረስን በተመለከተ ያሉ አስገዳጅ ህጎችን እንደምተነሳ አስታወቀች፡፡በፓስፊክ በምትገኘዉ በዚህች የደሴት ሀገር የተጠቂዎች ቁጥር 214 ሲደርስ ሶስት ሰዎች ህይወታቸዉ አልፏል፡፡

~ በታይላንድ የሚገኝ አንድ ጋዜጣ ፊሊፒንስን የኮሮና ቫይረስ ምድር ሲል ለህትመት ባበቃዉ ዘገባ ላይ መካተቱ የፊሊፒንስን ዜጎች እያስቆጣ ይገኛል፡፡በምስራቅ እስያ ከፍተኛ የቫይረሱ ስርጭት በፊሊፒንስ መኖሩ ለዘገባዉ መነሻ ቢሆንም የፊሊፒንስ ዜጎች በታይላንድ ሀገር የሚገኘዉ ጋዜጣ ይቅርታ እንዲጠይቅ እንፈልጋለን ብለዋል፡፡

~ በግሪክ በድጋሚ የኮሮና ቫይረስ ማገርሸቱን ተከትሎ የአቴንስ ሙዚየም እንዲዘጋ ዉሳኔ ተላለፈ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *