መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 5፣2012-የአፕል ዋና ስራ አስፈጻሚ ቲም ኩክ ከቢሊየነሮቹ ጎራ ተቀላቀለ

ግዙፉ የቴክኖሌጂ ተቋም የሆነዉ አፕል ገበያዉ ከፍ ማለቱን ተከትሎ የባለ አክስዮኖች ድርሻ ከፍ እንዲል አስችሏል፡፡ኩክ በዚህም መሰረት ካለፈዉ ዓመት የበለጠ 125 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር የበለጠ ድርሻን ማግኘት ችሏል፡፡

በዚህም መሰረት ቲክ ኩክ የቢሊየነሮቹን ጎራ እንዲቀላቀል አግዞታል፡፡ባሳለፍነዉ ሳምንት የፌስቡን መስራቹ ማርክ ዙከንበርግ ከ100 ቢሊየን ዶላር በላይ ሀብት ማካበቱ ይፋ መደረጉ አይዘነጋም፡፡

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ በበርካታ ኢንዱስትሪዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ቢያደርስም የቴክኖሎጂ ኩባንያ የሆኑት አፕል፣ፌስቡክ እና አማዞን ግን የትርፍ መቀዛቀዝ አላጋጠማቸዉም፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *