መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 7፣2012-የቀድሞ የጦር ጄነራል በዩጋንዳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታወቁ

የዩጋንዳ ጦር ጄነራል የነበሩት ሄነሪ ቱሙኩንዲ በሀገሪቱ በሚደረገው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ እንደሚሳተፉ አስታውቀዋል፡፡ጄነራሉ “ኪሶቦካ”በተባለ የምርጫ መቀስቀሻ ስያሜ የተጠቀሙ ሲሆን ይቻላል የሚል አቻ ትርጉም አለዉ፡፡

ሄነሪ ቱሙኩንዲ በቀጣዩ የዩጋንዳ ምርጫ ለማሸነፍ የሚያስችላቸዉን የተቀናጀ ዝግጅት እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ጄነራሉ ኤንቲቪ በተሰኘ የቴሊቪዥን ጣቢያ የምርጫ ቅስቀሳ ቪዲዮ ይፋ አድርገዋል፡፡

የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ይዌሪ ሙሴቪኒ ከዚህ ቀደም በምርጫ ቅስቀሳቸው ወቅት ራፕ ማቀንቀናቸዉ አይዘነጋም፡፡ለ34 ዓመታት ሙሴቬኒ ሀገሪቱን የመሩ ሲሆን በቀጣዩ ምርጫ ለማሸነፍ ዝግጁ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *