መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 7፣2012-የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ የምግብ ብክነትን ለማስቀረት እንዲቻል የንጹሃ ሳህን የተሰኘ ዘመቻ አስጀመሩ

የቻይናው ፕሬዝዳንት ሺ ጂፒንግ እንደተናገሩት ከሆነ የምግብ ብክነት በስፋት እየተስተዋለ በመሆኑ ብክነትን ልንከላከል ይገባል ብለዋል፡፡የሚመረተዉ ምግብ በቂ ሆኖ ሳለ በብክነት የተነሳ እጥረት እያጋጠመ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በአዲሱ መመሪያ መሰረት በዉሃን የሚገኙ የምግብ የኢንዱስትሪ ማህበራት ይፋ እንዳደረጉት አስር ሰዎች ዘጠኝ ምግብን ብቻ በማዘዝ ብክነትን ለመከላከል ወጥነዋል፡፡ኤን ሲቀነስ አንድ(N-1)የሚል ስያሜ ዘመቻዉ ተሰጥቶታል፡፡

እ.ኤአ. በ2015 የአለም የምግብ መርሃግብር ባወጣዉ ሪፖርት በቻይና በየአመቱ ከ17 እስከ 18 ሚሊየን ቶን ምግብ ለብክነት ይዳረጋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *