መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 8፣2012-በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የተነሳ ከከተማ ነዋሪዎች 45 በመቶ የሚሆኑት የገቢ ማጣት ጫና እንዳሳደረባቸዉ ተጠቆመ

የአለም ባንክ በሰራዉ የዳሰሳ ጥናት በስልክ ካነጋገራቸዉ የጥናቱ አባላት መካከል በኢትዮጲያ 45 በመቶ የከተማ ነዋሪዎች ለገቢ ማጣት ተዳርገዋል፡፡በተመሳሳይ ወረርሽኙ ባስከተለዉ ጫና 55 በመቶ በገጠር የሚኖሩ ዜጎች ለገቢ ማጣት መዳረጋቸዉን የዳሰሳ ጥናቱ ያመላክታል፡፡
በናይጄሪያ የአለም ባንክ በሰራዉ ተመሳሳይ የዳሰሳ ጥናት በወረርሽኙ የተነሳ 79 በመቶ ዜጎች የገቢ መቀነስ አጋጥሞናል ያሉ ሲሆን 42 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ከስራ ገበታቸዉ ተፈናቅለዋል፡፡

በአፍሪካ የ190 ሚሊየን ህዝብ ሀገር የሆነችዉ ናይጄሪያ እና የ102 ሚሊየን ህዝቦች ሀገር የሆነችዉ ኢትዮጲያ በህዝብ ብዛታቸዉ የአህጉሩ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል፡፡

የአለም ባንክ ሪፖርት እንደሚያሳየዉ በወረርሽኙ የተነሳ ከሰሀራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ከ13 እስከ 50 ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ለከፋ ረሃብ ሊጋለጡ ይችላል ይላል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *