መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 8፣2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

በኢትዮጲያ በእስር ላይ የሚገኘዉ የኬንያ ዜግነት ያለዉ ጋዜጠና በኮሮና ቫይረስ መጠቃቱ ተሰማ፡፡ጋዜጠኛ ያሲን ጁማ በቫይረሱ ስለመጠቃቱ ጠበቃዉ ከድር ቡሎ ተናግረዋል፡፡ከሌሎች ሁለት ኢትዮጲያዉያን ጋዜጠኖች ጋር የዘር ግጭት ማነሳሳት በሚል ክስ በቁጥጥር ስር ዉሎ ይገኛል፡፡

የቬንዝዌላ መዲና ካራካስ አዉራጃ ገዢ ዳሪዮ ቪቫስ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰማ፡፡የፕሬዝዳንት ኒኮላስ ማዱሮ የቅርብ አጋር ነበር ተብሏል፡፡

ወደ ዩናይትድ ኪንግደም ከስድስት ሀገራት የሚመጡ ዜጎች አስገዳጅ ለ14 ቀናት ወደ ለይቶ ማቆያ የመግባት ግዴታ እንዳለባቸዉ ተነገረ፡፡ከፈረንሳይ፣ኔዘርላንድና ሞናኮ የሚመጡ መንገደኞችን የሚመለከት ህግ ነዉ ፡፡

በሜክሲኮ ባለፉት 24 ሰዓት ተጨማሪ 627 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰማ፡፡የጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ መረጃ እንደሚያሳየዉ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 505,751 ሲደርስ የ 55,293 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

ሰሜን ኮርያ በደቡብ ኮርያ የድንበር ከተሞች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የጣለችዉን አስገዳጅ ህግ ማንሳቷን አስታወቀች፡፡

በህንድ በ24 ሰዓት ዉስጥ ብቻ 1,007 ሰዎች ህይወት በኮሮና ቫይረስ ያለፈ ሲሆን አጠቃላይ በህንድ የሟቾች ቁጥር 48,040 ደርሷል፡፡

የብራዚል ፕሬዝዳንት ጄር ቦርሴናሮ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ እቀባ ባለማድረጋችን የተነሳ ብራዚል ከበርካታ ሀገራት አንጻር የተሻለ ቁመና ላይ ትገኛለች ሲሉ ተናገሩ፡፡ፕሬዝዳንቱ ኢኮኖሚዉ እንዳይጎዳ በሚል አስገዳጅ ክልከላ ህግ እንዳይተገበር ማድረጋቸዉ ይታወሳል፡፡ብራዚል በወረርሽኙ የተነሳ ከ105 በላይ ዜጎቿን ህይወት አጥታለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *