መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 10፣2012-በመቂ ከተማ አንድ ወጣት ለእናቱ ያስገነባውን መኖሪያ ቤት የአረጋዊያን ማእከል አድርጓል!

ወጣት ያሬድ ኢሳያሥ ተወልዶ ያደገው በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን መቂ ከተማ ነው፡፡ ያሬድ በመቂ ከተማ ያስገነባው ባለ አንድ ፎቅ ህንፃ እና 12 ክፍሎች ያሉትን ሰርቪስ ቤት ያሰራው የእናቱ መኖሪያ ቤት እንዲሆን ነበር።

ሆኖም በብዙ ውጣ ውረድ ያሳዳገችኝ እናቴ በመጦሪያ እድሜዋ እንድትኖርበት ያስገነባሁት ቢሆንም አልተሳካም ይላል ያሬድ። የያሬድ እናትም ልጃቸው ወዳስገነባላቸው አዲስ ቤት ሳይገቡ ሞት ቀደማቸውና ወደ ዘላቂ ማረፊያቸው አመሩ።

“አጋጣሚው ሀዘኔን መሪር አድርጎታል” የሚለው ያሬድ “የእናቴን መልካምነት ሁሌም ለማስታወስ ስል ቤቱን የአረጋዊያን ማእከል ለማድረግ ወስኛለሁ” ይላል።

ማእከሉንም በእናቱ ስም እንዲጠራ በማድረግ “እልፍነሽ ሆርሳ የአረጋዊያን መኖሪያ ማዕከል” ብሎ መሰየሙን ገልጿል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *