መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 11፤2012 በሞቃዲሾ ሆቴል ውስጥ ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 7 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

ጥቃቱ በትላንትናው እለት የተፈፀመ ሲሆን ነሰባት ሰዎችን ሕይወት ሲነጥቅ ከ 20በላይ ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡

ታጣቂዎቹ በመኪና ላይ ያጠመዱትን ቦንብ በማፈንዳት ወደ ተኩስ ልውውጥ መግባታቸው ታውቋል፡፡

በሊዩ የባህር ዳርቻ በሚገኘው ኢሊት ሆቴል ለተሰነዘረው ጥቃት አልሻባብ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታውቋል፡፡

Ak-47 የተሰኘ ጠመንጃ የታጠቁት 4 ታጣቂዎች መገደላቸው ተረጋግጧል፡፡

ጥቃቱ በሆቴል ላይ ሲፈፀም በርካታ የመንግስት ባለስልጣናት ውስጥ እንደነበሩ ተነግሯል፡፡ የሆቴሉ ባለቤት አብዱላሂ ሞሃመድ ኖር ሲሆን የቀድሞ የሶማሊያ የፋይናንስ ሚኒስትር ነበሩ፡፡

በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *