መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 11፤2012-የብስራት ማለዳ አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች

~ የብራዚሉ ፕሬዝደንት ጄር ቦርሴናሮ ባለቤት እና ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ቦርሴናሮ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ ተባለች፡፡ ፕሬዝዳንቱ በቫይረሱ መያዛቸው የሚታወስ ሲሆን ለቀዳማዊት እመቤቷ በተደረገ ተደጋጋሚ ምርመራ ነፃ ተብላለች፡፡ የ 38 ዓመቷ ቀዳማዊት እመቤት ሚሼል ቦልሶናሮ የፕሬዝደንቱ ፀሃፊ ነበረች፡፡ ለፕሬዝደንቱ ሶስተኛ ትዳራቸው ሲሆን ከቀድሞ ፀሃፊያቸው ከአሁኗ ባለቤታቸው ላውራ የተባለች ሴት ልጅን አግኝተዋል፡፡

~ በህንድ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከ 50ሺ በለጠ፡፡ ከ 2.65ሚሊየን የቫይረሱ ተጠቂ ባለባት ህንድ የ 50‚921 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡

~ በሜክሲኮ በኮቪድ-19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር ከ 522 ሺ ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር 56‚757 ደርሷል፡፡

~ የሜክሲኮ ፕሬዝደንት አንድሬስ ማኑኤል ሎፔዝ አብራዶር የተያዘው 2020 ዓመት ሳያልቅ የኮሮና ቫይረስ የክትባት መድሃኒትን ሀገራቸው እንደምታገኝ ይፋ አድርገዋል፡፡

~ ቻይና የመጀመሪያው በተባለው የኮቪድ-19 የክትባት መድሃኒት እውቅና ሰጠች፡፡ የክትባት መድሃኒቱ Ad5-nCoV የተሰኘ ሲሆን ካንሲኖ እና በቻይና ጦር የኢንፌክሽን በሽታ ኤክስፐርቶች የተሰራ ነው፡፡

~ የቀድሞ የቦሊቪያ ፕሬዝደንት ኢቮ ሞራሌስ ሴት ልጅ ኢስቴር ሞራሌስ በ 70 ዓመቷ በኮሮና ቫይረስ ህይወቷ ማለፉ ተሰማ፡፡ ሞራሌስ እንደ እናቴ ነበረች ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የቀድሞ የቦሊቪያ ፕሬዝደንት ኢቮ ሞራሌስ በስደት ሜክሲኮ ይገኛል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *