መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 11፤2012-የተባበሩት ዓረብ ኤምሬት የስልክ አገልግሎት ከእስራኤል ጋር መጀመሯ ሲሰማ የሀገራቱን ግንኙነት የሚያሻሻል ስራዎችን ይፋ አድርጋለች

የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትን ለመጀመሪያ ጊዜ የስልክ አገልግሎት ወደ እስራኤል እንዲጀመር ስታደርግ የታገዱ የእስራኤል ድህረ-ገፆች ክፍት ተደርገዋል፡፡

በሀገራቱ መካከል የስልክ ልውውጥ መፈቀድን ተከትሎ የኢምሬትስ ሼኪህ አብዱላሂ ቢን ዛያድ አል ናህያአን ከእስራኤል አቻቸው አሽ ኬንዚ ጋር የስልክ ልውውጥ አድርገዋል፡፡ ሀገራቱ ባሳለፍነው ሳምንት የዲፕሎማሲ ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ውል ማሰራቸው ይታወሳል፡፡

በተያዘው ሳምንት የቀጥታ በረራ ፣ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ስምምነት በአቡዳቢ እና ቴላቪቭ መካከል ይፈረማል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፍልስጤማውያኑን ያበሳጨ ድርጊት ሆኗል፡፡ እንዲሁም ኢምሬቶችለቀጠናው ስጋት የሆነ ስምምነት ላይ ደርሰዋል ስትል ኢራን ከሳለች፡፡

የተባበሩት ዓረብ ኢምሬትስ ከእስራኤል ጋር የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዳሻሻለች ሁላ በቀጣይ ባህሬን እና ኦማን ይህንን ድርጊት ይከተላሉ ስትል እስራኤል ተናገረች

ከገልፍ ሀገራቱ ባህሬን እና ኦማን ተመሳሳዩን ድርጊት እንደሚፈፅሙ ይጠበቃል ስትል እስራኤል ተናግራለች፡፡

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታናሁ ከኦማን እና የሱዳን መሪዎች ጋር ባለፉት ሁለት ዓመታት መምከራቸው ይታወሳል፡፡

ወደዚህ የሰላም አጥር ውስጥ በርካታ ሀገራት መምጣት እንደሚጀምሩ አምናለሁ ሲሉ ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታናሁ ለካቢኔያቸው ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *