መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 12፤2012 -የቀድሞ የሲአይኤ ሰላይ ለቻይና ይሰልል ነበረ በሚል ክስ ተመሰረተበት

የቀድሞ የማዕከላዊ የደህንነት ኤጀንሲና የፌደራል የደህንነት ቢሮ አባል የነበረዉ ሰዉ ለቻይና ይሰልል እንደነበር የአሜሪካ የፍትህ ቢሮ አስታዉቋል፡፡የ67 ዓመቱ አሌክሳንደር ቺንግ ማ ለዉጪ መንግስታት ብሄራዊ የመከላከያ መረጃን ያቃብል ነበር ተብሏል፡፡

በማ ላይ የቀረበበት ክስ እንደሚያስረዳዉ ከሆነ በ2014 እና በ2016 ዓመት ቢያንስ ከአምስት የቻይና የደህንነት ባለስልጣናት ጋር በሆንግ ኮንግ መገናኘቱ ይፋ ተደርጓል፡፡በተለይ በመከላከያ ዙርያ በርካታ ሚስጥሮች አፈትልከዉ እንዲወጡ ስለማድረጉ ተነግሯል፡፡አቃቢ ህግ በተጨማሪነት ማ 50ሺ የአሜሪካን ዶላር ገንዘብ በድብቅ ሲቆጥር የሚያሳይ ቪዲዮ አለኝ ብሏል፡፡

ማ በተከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ የሚባል ከሆነ የእድሜ ልክ እስር ይጠብቀዋል፡፡የደህንነት ሀይሎች ዋንኛ አላማ የሀገርን ደህንነት ያለ እረፍት መጠበቅ ነዉ ሲል ኤፍቢአይ ይፋ አድርጓል፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *