መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 13፤2012-የማሊው ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬታ ከስልጣናቸው መውረዳቸው ተሰማ

ፕሬዝዳንቱ በትናንትናው እለት በወታደሮች መከበባቸውን ተከትሎ ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ተገደዋል፡፡

ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ኬታ በሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ ባስተላለፉት መልዕክት እኔን በስልጣን ላይ ለማስቀጠል ሲባል፡፡ የማንም ደም መፍሰስ የለበትም ብለዋል፡፡

በመዲናዋ ባማኮ አቅራቢያ በሚገኝ የጦር ሰፈር ውስጥ ፕሬዝደንት ኢብራሂም ኬታ እና ጠቅላይ ሚኒስቴር ሲሴ እንዲቆዩ መደረጉም ተሰምቷል፡፡

በጦሩ ጣልቃ ገብነት ፕሬዝዳንቱ ከስልጣን መነሳታቸው የማሊ ጎረቤቶች እና ፈረንሳይ ተቃውመውታል፡፡ እ.ኤ.አ በ 2018 በሁለተኛ ዙር ምርጫ በማሸነፍ ስልጣናቸውን ያስቀጠሉት ኬታ በሙስና ፣ በሀብት አስተዳደር ብክነት እና የጂሃዲስቶችን ጥቃት ማስቆም አልቻሉም በሚል ሲተቹ ቆይተዋል፡፡

ባለፉት ጥቂት ወራትም በወግ አጥባቂው ኢማም እና በተቃዋሚዎች ጥምረት የሚመራው ማሀሙድ ዲኮ አማካኝነት ስለለውጥ ከፍተኛ ጥያቄ ሲቀርብ ቆይቷል፡፡

ጠ/ሚ እና ፕሬዝደንቱን በቁጥጥር ስር በማዋል ከስልጣን እንዲወርዱ የተደረገው የወታደሮቹ ግፊት በኮሎኔል ማሊክ ዲዋ ተመርቷል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና የአፍሪካ ህብረት የወታደሮቹን ድርጊቱን ኮንነዋል፡፡

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *