መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 19፣2012-እስራኤል በጋዛ በፈጸመችዉ የአየር ላይ ጥቃት አራት ፍልስጤማዉያን ተገደሉ

የእስራኤል ጦር በተዋጊ ጀቶች በምስራቃዊ የጋዛ ሰርጥ በፈጸመዉ ጥቃት አራት ፍልስጤናዉያን መገደላቸዉ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ግለሰቦቹ በጋዛ ከተማ እንደነበሩ የፍልስጤም ነጻ አዉጪ ሀማስ አስታዉቋል፡፡
እስራኤል ጥቃቱን በተመለከተ ስለግለሰቦቹ መገደል የተናገረችዉ ነገር ባይኖርም በተሰነዘረባት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ መስጠቷን ይፋ አድርጋለች፡፡
በሌላ መረጃ በጋዛ ሰርጥ ሰላም እንዲመጣ ያለመ የሁለትዮሽ ዉይይት ለማደረግ የእስራኤል ከፍተኛ ባለስልጣናት ኳታር ዶሃ መግባታቸዉ ተረጋግጧል፡፡በእስራኤል ልዑክ ዉስጥ የሞሳድ የደህንነት ኃላፊና የእስራኤል ጦር የደቡባዊ ሀላፊ ይገኙበታል፡፡
በእስራኤልና በሀማስ መካከል ያለዉ ዉጥረት እንዲያበቃ ግብጽ ሁለቱ አካላት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ እንዲደርሱ ላሸምግል ብትልም ቁልፍ ሚና እንዳላት የታመነችዉ ኳታር ሆናለች፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *