መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 19፣2012-በህንድ በከባድ አደጋ ከተደረመሰ ህንጻ ውስጥ ከ60 በላይ ሰዎች በህይወት መትረፋቸዉ ተሰማ

አደጋዉ ትናንትና ከሰዓት የደረሰ ሲሆን በህንድ የፋይናንስ ከተማ ከሆነችዉ ሙምባይ አቅራቢያ ያጋጠመ ነዉ፡፡የተደረመሰዉ ህንጻ ባለ አምስት ወለል ሲሆን ማሃዳ በተባለዉ አዉራጃ ይገኛል፡፡
በህንጻዉ ዉስጥ 200 ያህል ሰዎች እንደሚኖሩም ተነግሯል፡፡እስካሁን በተረጋገጠ መረጃ አንድ ግለሰብ ህይወቱ ሲያልፍ 30 ሰዎች ክፉኛ ቆስለዋል፡፡አደጋዉ እንዴት ሊያጋጥም እንደቻለ ማብራሪያ አልተሰጠዉም፡፡
ሆኖም በህንድ በተደጋጋሚ የህንጻ መደርመስ አደጋ እንደሚያጋጥም መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡በ2017 ዓመት ብቻ ብሄራዊ የወንጀል ቢሮ ባወጣዉ መረጃ መሰረት በህንድ 1.161 ህንጻዎች ተደርምሰዉ ከ1200 በላይ ሰዎችን ህይወት ነጥቋል፡፡
ይህንኑ መሰል አደጋ በህንድ ዝናባማ ወቅት በሆነዉ ከሰኔ እስከ መስከረም ባሉት ወራት ያጋጥማል፡፡በተያዘዉ ዓመት ዝናብ ካስከተለዉ የጎርፍና የመሬት መንሸራተት አደጋ በህንድ ከ800 በላይ ሰዎች ህይወታቸዉን አጥተዋል፡፡
በሚኪያስ ጸጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *