መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 19፣2012-20 ኩንታል ጤፍ በሀሰተኛ የብር ኖቶች የገዙት ግለሰቦች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

ድርጊቱ የተፈፀመው በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛምን ወረዳ ሊቫኖስ ቀበሌ ልዩ ቦታው ሮቢት እየተባለ በሚጠራው ቦታ ነሐሴ 18/2012 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት ነው።

1ኛ ተጠርጣሪ አብርሃም ሙሉ፣2ኛ ሻምበል የሹም፣ 3ኛ አሸብር አላምረው የተባሉ ግለሰቦች የጤፍ ነጋዴ ከሆነው አቶ መሰረት አስቻለ 20 ኩንታል ጤፍ በመግዛት ብር ሲረካከቡ የጤፍ ነጋዴው ሀሰተኛ የብር ኖት እንደሆነ በመረዳት ለፖሊስ ጥቆማ ሰጥቷል።

ፖሊስም ጥቆማውን ተቀብሎ ተጠርጣሪዎችን እጅ ከፈንጅ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል።

ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር በዋሉበት ወቅትም፦
1ኛ፦90ሺ 1 መቶ ሀሰተኛ የብር ኖት፤2ኛ፦13ሺ 7 መቶ ህጋዊ የብር ኖት፤3ኛ፦ ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ ከ6 መሰል ጥይት፤4ኛ፦ስድስት ተንቀሳቃሽ ስልክ ተገኝቶባቸዋል።
የጎዛምን ወረዳ ፖሊስም ምርመራ በማጣራት ላይ ይገኛል፡፡

የወረዳው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኃላፊ ረዳት ኢንስፔክተር ፀጋዬ ጋሹ እንደገለፁት በመጭው አዲስ አመት ወቅት ህብረተሰቡ ልዩ ልዩ ግብይቶችን ሲያከናውን ለእንዲህ አይነቱ የወንጀል ድርጊት ሰለባ እንዳይሆን አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥምም ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት ወንጀልን የመከላከል ተግባሩን እንዲወጣ
ጥሪ አስተላልፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *