መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 20-2012-በህንድ ባለቤቴ ከመጠን በላይ ጥሩ ሰው ሆነብኝ ያለች ሚስት ፍቺ መፈጸም እንደምትፈልግ ለፍርድ ቤት አሳዉቃለች

በህንድ ፓርዲያሽ ግዛት ነዋሪ የሆነችዉ ግለሰብ ለአካባቢዉ የሸሪያ ፍርድ ቤት ባቀረበችዉ ጥያቄ ባለቤቴ ከመጠን በላይ ጥሩ ሰዉ ነዉ፣አብዝቶ ይወደኛል፣የቤት ዉስጥ ስራ ቀድሞ ያከናዉናል ይህንን ደግሞ ፈጽሞ ልቀበለዉ አልችልም ስትል ተናግራለች፡፡ለፍርድ ቤቱ እንዲህ ዓይነት ጉዳይ አዲስ ቢሆንም በኢምሬትስ በተመሳሳይ ክስ ሚስት ባሏን ፈታለች፡፡
ጥንዶቹ ለ18 ወራት በፍቅር ስለመቆየታቸዉ ከፍርድ ቤቱ ዉሎ የተሰማ ሲሆን በቀጣይ ሳምንት ጉዳያቸዉ ይለይለታል ተብሎ ይጠብቃል፡፡ፍቅር አበዛብኝ መሬት አይንካሽ አለኝ በህንድ ለፍቺ ምክንያት ሆነ ቢባልም የፍቺ መጠን ዝቅተኛ ከሆነባቸዉ ሀገራት መካከል ህንድ ቀዳሚ ናት፡፡በሀገረ አሜሪካ በየ አንድ ሰዓት ልዩነት 100 ፍቺ ይፈጸማል፡፡
በፊሊፒንስ ፍቺ መፈጸም ህገ ወጥ ተግባር ሲሆን በማሌዥያ ግን በአጭር የጹሁፍ መልእክት ቴክስት(ኤስኤምኤስ ) በመጻፍ ብቻ ፍቺ መፈጸም ይቻላል፡፡ በመላዉ ዓለም ፍቺ የሚፈጸምበት አማካይ ወር ከ18 ወራት የጋብቻ ቆይታ በኃላ ነዉ፡፡

በስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *