መደበኛ ያልሆነ

ነሐሴ 21-2012-የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከጆ ባይደን ጋር ከሚኖራቸው ክርክር አስቀድሞ የእጽ መጠቀም አለመጠቀሙ ምርመራ ያድርግ ሲሉ ተናገሩ

በቀጣይ ወር ለሚደረገዉ የዲሞክራቶቹ እና የሪፓብሊካን እጩ ክርክር በፊት ሁለታችንም እጽ መዉሰድ አለመዉሰዳችንን በተመለከተ ምርመራ ይደረግልን ሲሉ ትራምፕ ጠይቀዋል፡፡ትራምፕ ይህንን ያሉ ከዋሽንግተን ኤግዛማይነር ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ነዉ፡፡
ትራምፕ ሲናገሩ ጆ ባይደን ከዲሞክራቶች ጋር በነበረዉ የእጩ ክርክር ወቅት በድንገት አቅሙ ሲሻሻል አስተዉያለዉ ምናልባትም የአነቃቂ እጽ ወስዶ ሳይሆን አይቀርም ሲሉ አስታዉቀዋል፡፡
በወርሃ ህዳር መጀመሪያ ከሚካሄደዉ የአሜሪካ ምርጫ አስቀድሞ ባይደን እና ትራምፕ ለሶስት ጊዜ ያህል የፊት ለፊት ክርክር እንደሚዲርጉ ይጠበቃል፡፡
በ2016 ትራምፕ ተፎካካሪያቸዉ ለነበረችዉ ሂላሪ ክሊንተን ሊያነሳሳት ስለሚችል ከክርክራችን በፊት የእጽ ምርመራ እንድታደርግ መጠየቃቸዉ ይታወሳል፡፡74 ዓመቱ ትራምፕ ከ77 ዓመቱ ባይደን ጋር ለቀጣዩ የአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ብርቱ ፉክክር እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡
በሚኪያስ ፀጋዬ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *